Posts

ደህና ሁኚ

የተሳሰርንበትን ገመድ ከበጠስሽው ዘንዳ፣ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። ገመድ የለም ከደረቴ፣ ያሰርኩበት ሲባጎም የለምና ከእጄ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። የት ሄደች ካሉኝ ፈታኋት እላቸዋለሁ። 

ሔዋኔ

Image
እንዲሁ እንደነቃሁ በአይኖቼ መገለጥ መሀል በቅዠት የተዋዛ፣ በራዕይ የተለወሰ ህልም አያለሁ፡፡ የሚጣፍጥ ህልም፣ በፀጋ የሚያላብስ ህልም፡፡ እንዲሁ እንደነቃሁ . . . እርሷን አያታለሁ፡፡

አቦነሽ አድነው “አርቲስት” የሚለው መጠርያ ይገባታል?

Image
ቀደም ሲል በተለየ ቅላፄዋና በባህል ሙዚቃዎቿ የምናውቃት አቦነሽ አድነው “ከዚህ በኋላ ዓለም ከአንደበቴ በሚወጣ ዘፈን አትደንስም ይልቁንስ ጩኸቴ፣ ቅኔ እና ዜማዬ የምስጋና ብቻ ነው” ብላ አዲስ የመዝሙር ስራዎቿን ይዛ ሰሞኑን ብቅ ማለቷ የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ሲያነጋግር የሰነበተ ጉዳይ ነበር፡፡ መቼም ሰው ከአካባቢ ተፅንዖ፣ ከዓለም ዳንኪራ፣ ከከንቱ ውዳሴና ጭብጨባ አምልጦ  ሁለመናን ለፈጣሪ ሲሰጥ ማየት መንፈሳዊ ቅንዓት ከማሳደሩም በላይ ያበረታል፡፡ ይህን ስል ግን ዓላማዬ ያልተገባ የሰው ምስጋና ለአቦነሽ ለመስጠት ወይንም ብላቴናዋን ዘማሪት “ቅድስት” ብሎ ለመጥራት አይደለም፡፡

አንዳንድ ብሽቅ ሰዎች

Image
ቅዳሴ መሃል ነው፡፡ “በንሰሃ ውስጥ ያላችሁ ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ” በሚለው የካህን ትዕዛዝ መሰረት በመቅደሱ ውስጽ ካሉት ጀምሮ ከደጀ ሰላሙ ቅጽር ውጪ እስካሉት ሰዎች ድረስ ግማሹ ከወገቡ ጎንበስ ከጉልበቱ ሸብረክ ብሎ የሁለት እጆቹን መዳፍ ለፈጣሪው እያሳየ ግማሹ ደግሞ በግንባሩ ተደፍቶ በፍፁም ፀጥታ ተውጠዋል፡፡ በድምፅ ማጉያው ከሚሰማው ከካህኑ የእግዚዮታ ድምፅ ውጭ ምንም ነገር አይሰማም አይንቀሳቀስም፡፡

ኢትዮጵያ ማለት እኔ ነኝ - ይድረስ ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች

Image
ይድረስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላልተደሰታችሁ እና ኢትዮጵያን እናንተ መልካም ነው ወዳላችሁት ጎዳና ለመውሰድ ለምትጥሩ የተቃዋሚም ሆነ የገዢው ፓርቲ ፖለቲከኞች፡፡ ይህ መልዕክት ያሰባችሁትን ሁሉ ለማሳካት ሊፈቅድላችሁም ሆነ ሊከለክላችሁ ከሚችለው ከመላ የኢትዮጵያ ህዝብ መሀል የአንዱ ድምፅ ነው፡፡

አከራዮቼ 1

Image
እንደው መታደል ሆኖ ከኢትዮጵያዊ እናት ተፈጠርኩኝ እንጂ ወላጆቼ ፈርዶባቸው ፈረንጅ ቢሆኑ ኖሮ እድሜዬ ለአቅመ ሸክም በደረሰ በዚያ ወቅት (በ19 ዓመቴ ማለት ነው) “ሌላ ቤት ተከራይ አሊያም ኪራይ ክፈል” ይሉኝ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ግን እኔ ራሴን መቻል ያሰኘኝ ወቅት ስለነበር እናቴን ሔጄ " ራሴን አሸክሚኝ" ስላት አንድ ቃል ነበር ከአፏ የወጣው “አትቅበጥ” የሚል፡፡ አዲስ ቦታ፣ አዲስ ሰው፣ አዲስ ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ አንድ ነገር ወይንም አንድ ቦታ ላይ ችክ ማለት አልችልበትም፡፡ ስልቹ ነገር ነኝ፡፡ የምሰራበት ቦታ ላይ ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር ካልቻልኩ ቀኑን መግፋት ያቅተኛል፡፡ ተደጋጋሚ(Routine) ነገሮችን እንደመፈፀም የሚያሳምመኝ ነገር እስካሁን የለም፡፡ ለነገሩ ስራ ላይ ብቻ ሳይሆን ቤት ኪራይ ላይም እንዲሁ ነኝ፡፡ ባለፉት በአስር አመታት ውስጥ እንኳን ስምንት ቤቶችን ለዋውጫለሁ፡፡ ኪራይ እስከሆነ ድረስ ምን አንድ ቦታ ላይ አስቸከለኝ?

እኔ እግዚአብሔር እና ስሜ

Image
በጭለማው መሃል ድንገት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማብሪያ ማጥፊያውን ተጭኖ ጭለማውን ገሰሰው፡፡ አናቴ ደንግጣ እያማተበች በዚያ ለሊት የሚያፈጥባትን ሰውዬ መልሳ ትመለከተዋለች፡፡ “ምንድነው ይሔ?” አላት ሆዷን በሌባ ጣቱ እየጠነቆለ፡፡ እንደመተንፈስ አለችና “እኔንጃ” አለች ፊቱን ላለማየት አቀርቅራ፡፡ “እኔንጃ? ምንማለት ነው እኔንጃ? ኪኒን እንድትወስጂ ተስማምተን እየዋጥሽ አልነበር እንዴ?” በዚያ ፀጥ ባለ ሌሊት የእርሱ ድምፅ ብቻውን እንደመብረቅ ይጮሃል፡፡ “አዎ ኪኒኑንማ እየዋጥኩ ነው” አሁንም እንዳቀረቀረች ነው፡፡ “እና?!?!?” በይበልጥ አምባረቀ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ የምትችል አልመስል አላት ቢመታትም ጠንካራ ክንዱን ለመቻል ተዘጋጅታ “እንግዲህ ኪኒኑ አልሰራልኝም ማለት ነው ያለዚያማ እንዴት ልፀንስ እችላለሁ?” አለችው ተኮሳትራ፡፡ እንግዲህም ይህ ቅፅበት ነበር  ለእኔ የህይወት መጀመርያ ለወላጆቼ ደግሞ የመጨረሻዋ ቀን የሆነችው፡፡ አቶ “አባት” እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ የሰውና የጊዜ ክፉ የገጠማት እናቴም እኔን በሆዷ የሆነውን ሁሉ በልቧ ይዛ ብቸኛ ሆነች፡፡ አላማዬ የህይወት ታሪኬን ልነግራችሁ አይደለም የስሜን አመጣጥ ለማብራራት ይሔን ታሪክ መንገር ስላስፈለገኝ እንጂ፡፡