ደህና ሁኚ Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps - August 07, 2019 የተሳሰርንበትን ገመድ ከበጠስሽው ዘንዳ፣ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። ገመድ የለም ከደረቴ፣ ያሰርኩበት ሲባጎም የለምና ከእጄ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። የት ሄደች ካሉኝ ፈታኋት እላቸዋለሁ። Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
አከራዮቼ 1 - November 01, 2012 እንደው መታደል ሆኖ ከኢትዮጵያዊ እናት ተፈጠርኩኝ እንጂ ወላጆቼ ፈርዶባቸው ፈረንጅ ቢሆኑ ኖሮ እድሜዬ ለአቅመ ሸክም በደረሰ በዚያ ወቅት (በ19 ዓመቴ ማለት ነው) “ሌላ ቤት ተከራይ አሊያም ኪራይ ክፈል” ይሉኝ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ግን እኔ ራሴን መቻል ያሰኘኝ ወቅት ስለነበር እናቴን ሔጄ " ራሴን አሸክሚኝ" ስላት አንድ ቃል ነበር ከአፏ የወጣው “አትቅበጥ” የሚል፡፡ አዲስ ቦታ፣ አዲስ ሰው፣ አዲስ ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ አንድ ነገር ወይንም አንድ ቦታ ላይ ችክ ማለት አልችልበትም፡፡ ስልቹ ነገር ነኝ፡፡ የምሰራበት ቦታ ላይ ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር ካልቻልኩ ቀኑን መግፋት ያቅተኛል፡፡ ተደጋጋሚ(Routine) ነገሮችን እንደመፈፀም የሚያሳምመኝ ነገር እስካሁን የለም፡፡ ለነገሩ ስራ ላይ ብቻ ሳይሆን ቤት ኪራይ ላይም እንዲሁ ነኝ፡፡ ባለፉት በአስር አመታት ውስጥ እንኳን ስምንት ቤቶችን ለዋውጫለሁ፡፡ ኪራይ እስከሆነ ድረስ ምን አንድ ቦታ ላይ አስቸከለኝ? ሙሉውን አስነብበኝ »
እኔ እግዚአብሔር እና ስሜ - October 05, 2012 በጭለማው መሃል ድንገት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማብሪያ ማጥፊያውን ተጭኖ ጭለማውን ገሰሰው፡፡ አናቴ ደንግጣ እያማተበች በዚያ ለሊት የሚያፈጥባትን ሰውዬ መልሳ ትመለከተዋለች፡፡ “ምንድነው ይሔ?” አላት ሆዷን በሌባ ጣቱ እየጠነቆለ፡፡ እንደመተንፈስ አለችና “እኔንጃ” አለች ፊቱን ላለማየት አቀርቅራ፡፡ “እኔንጃ? ምንማለት ነው እኔንጃ? ኪኒን እንድትወስጂ ተስማምተን እየዋጥሽ አልነበር እንዴ?” በዚያ ፀጥ ባለ ሌሊት የእርሱ ድምፅ ብቻውን እንደመብረቅ ይጮሃል፡፡ “አዎ ኪኒኑንማ እየዋጥኩ ነው” አሁንም እንዳቀረቀረች ነው፡፡ “እና?!?!?” በይበልጥ አምባረቀ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ የምትችል አልመስል አላት ቢመታትም ጠንካራ ክንዱን ለመቻል ተዘጋጅታ “እንግዲህ ኪኒኑ አልሰራልኝም ማለት ነው ያለዚያማ እንዴት ልፀንስ እችላለሁ?” አለችው ተኮሳትራ፡፡ እንግዲህም ይህ ቅፅበት ነበር ለእኔ የህይወት መጀመርያ ለወላጆቼ ደግሞ የመጨረሻዋ ቀን የሆነችው፡፡ አቶ “አባት” እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ የሰውና የጊዜ ክፉ የገጠማት እናቴም እኔን በሆዷ የሆነውን ሁሉ በልቧ ይዛ ብቸኛ ሆነች፡፡ አላማዬ የህይወት ታሪኬን ልነግራችሁ አይደለም የስሜን አመጣጥ ለማብራራት ይሔን ታሪክ መንገር ስላስፈለገኝ እንጂ፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ »
Comments
Post a Comment