የመጀመርያ
(በውሸት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ዕውነተኛ ታሪክ) ይህቺን ሚጢጢ ጥሁፍ እንድጥፋት የኮረኮረኝ ከባዱ ጦማሪ Naod ቤተሥላሴ በ “ናዖድ ኢትዮጵያዊ” ጦማሩ ላይ “ በአሜሪካ ሁሉ ነገር ‹‹ የመጀመርያ › › ባይሆንም በሚል ርዕስ አሜሪካኖች የመጀመሪያ ለመባል ትልልቅ ደንጊያዎችን እንዴት እንደሚያንከባልሉ ደስ በሚል ቋንቋ የገለፀውን ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ ናዖድ እንደገለፀው አሜሪካኖች ሩጫ ተወዳድሮ መጨረሻ ስለወጣ አሜሪካዊ ሯጭ ለመዘገብ መጀመርያ ‹ አንደኛ › ወይም ‹ የመጀመርያው › የሚሆንበት መንገድ ይፈለግለታል፡፡ ከጥቂት ምርመራ በኋላ ወይ በዕድሜው፤ ወይ በጾታው፤ ወይ በትምህርት ደረጃው፤ ወይ በመጣበት ሀገር፤ ወይ መጨረሻ በወጣበት ሰዓት የመጀመሪያ ሰው እንደሆነ ሲረጋገጥ ‹‹ በዚያ ሰዓት ለመግባት የመጀመርያው የሰባ ዓመት ዓዛውንት እንደሆነ ይዘገባል :: ታዲያ የናዖድን ፅሁፉን አንብቤ ስጨርስ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “በእኛ ቤት ታሪክ ውስጥ ሁለተኛ ልጅ በመሆን የመጀመሪያው ነኝ” ያለው ትዝ አለኝና ማሪኝ አሜሪካ አልኩ በልቤ::
Comments
Post a Comment