Posts

እኔ እግዚአብሔር እና ስሜ

Image
በጭለማው መሃል ድንገት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማብሪያ ማጥፊያውን ተጭኖ ጭለማውን ገሰሰው፡፡ አናቴ ደንግጣ እያማተበች በዚያ ለሊት የሚያፈጥባትን ሰውዬ መልሳ ትመለከተዋለች፡፡ “ምንድነው ይሔ?” አላት ሆዷን በሌባ ጣቱ እየጠነቆለ፡፡ እንደመተንፈስ አለችና “እኔንጃ” አለች ፊቱን ላለማየት አቀርቅራ፡፡ “እኔንጃ? ምንማለት ነው እኔንጃ? ኪኒን እንድትወስጂ ተስማምተን እየዋጥሽ አልነበር እንዴ?” በዚያ ፀጥ ባለ ሌሊት የእርሱ ድምፅ ብቻውን እንደመብረቅ ይጮሃል፡፡ “አዎ ኪኒኑንማ እየዋጥኩ ነው” አሁንም እንዳቀረቀረች ነው፡፡ “እና?!?!?” በይበልጥ አምባረቀ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ የምትችል አልመስል አላት ቢመታትም ጠንካራ ክንዱን ለመቻል ተዘጋጅታ “እንግዲህ ኪኒኑ አልሰራልኝም ማለት ነው ያለዚያማ እንዴት ልፀንስ እችላለሁ?” አለችው ተኮሳትራ፡፡ እንግዲህም ይህ ቅፅበት ነበር  ለእኔ የህይወት መጀመርያ ለወላጆቼ ደግሞ የመጨረሻዋ ቀን የሆነችው፡፡ አቶ “አባት” እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ የሰውና የጊዜ ክፉ የገጠማት እናቴም እኔን በሆዷ የሆነውን ሁሉ በልቧ ይዛ ብቸኛ ሆነች፡፡ አላማዬ የህይወት ታሪኬን ልነግራችሁ አይደለም የስሜን አመጣጥ ለማብራራት ይሔን ታሪክ መንገር ስላስፈለገኝ እንጂ፡፡

የትኛው ድሮ

Image
እድሜያቸው ዘጠና ዓመት የሞላቸውን አዛውንት ስለድሮ ብንጠይቃቸው ያለምንም ጥርጥር ከስልሳ አመት በፊት ስላለው ነገር ያጫውቱናል፡፡ የሀምሳ አመት ሽማግሌንም እንዲሁ ብንጠይቅ ከሀያ አምስት አመት በፊት ስላለው ጉዳይ ነው የሚነግሩን፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ የድሮ ትርጉሙ እንደ አጫዋቹ ይለያያል ማለት ነው፡፡

በየቀኑ መታጠብ ዋና አያስችልም

Image
ፈረስ መጋለብ የጀመርኩ ዕለት እንዴት ፈርቼ እንደነበር ልነግራችሁ አልችልም ግን ዕድሜ ለሃይሌ ሩት ጎትጉቶ ለወሰደኝ እና ላስተማረኝ ብዙም ሳልቆይ ነበር ያለፍርሃት በፍጥነት መጋለብ የጀመርኩት፡፡ ወዳጄ ፍቅሩ ታድያ አዲስ አበባ ውስጥ ፈረስ መጋለቢያ/መማርያ/ ቦታ እንዳለ ስነግረው በደስታ ነበር የፈነጠዘው፡፡ ችግሩ ግን ጊዜ አግኝቶ ይዠው ለመሔድ አለመቻሌ ነበር፡፡

ስደተኛ ቃላት

አንድ ቀን አዲስ አበባ ከጋናዊው ወዳጄ ጋር መረቅ የሆነ ጨዋታ እየተጫወትን በየአይነት እየበላን ነበር፡፡ ምሳችን ቢያልቅም ጫወታችንን ላለማቋረጥ አብረን ወደ እጅ መታጠቢያው እየተሳሳቅን አመራን፡፡ እጄን ወደ ውሃው ሰንዝሬ እየተለቃለቅኩ ቀድመውን ከሚታጠቡት ሰዎች መሀል አንደኛውን ሳሙናውን እንዲያቀብለን ጠየቅኩትና ወደጨዋታዬ ልመለስ ስል ይህ ጋናዊ ወዳጄ በመገረም አይነት ሰውየውን ምን እንዳልኩት በእንግሊዝኛ ጠየቀኝ እኔም ሳሙናውን አቀብለኝ እንዳልኩት በአማርኛ ስነግረው በጣም ተደንቆ ሳሙና የሚለውን ቃል እንደሚያውቀውና እሱ ከመጣበት ጋና ውስጥ ያለ አንድ ብሔርም በተመሳሳይ ይህንን መታጠቢያ ሳሙና ብለው እንደሚጠሩት ነገረኝ፡፡

የመጀመርያ

(በውሸት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ዕውነተኛ ታሪክ) ይህቺን ሚጢጢ ጥሁፍ እንድጥፋት የኮረኮረኝ ከባዱ ጦማሪ Naod ቤተሥላሴ በ “ናዖድ ኢትዮጵያዊ” ጦማሩ ላይ “ በአሜሪካ ሁሉ ነገር ‹‹ የመጀመርያ › › ባይሆንም  በሚል ርዕስ አሜሪካኖች የመጀመሪያ ለመባል ትልልቅ ደንጊያዎችን እንዴት እንደሚያንከባልሉ ደስ በሚል ቋንቋ የገለፀውን ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ ናዖድ እንደገለፀው አሜሪካኖች ሩጫ ተወዳድሮ መጨረሻ ስለወጣ አሜሪካዊ ሯጭ ለመዘገብ መጀመርያ ‹ አንደኛ › ወይም ‹ የመጀመርያው › የሚሆንበት መንገድ ይፈለግለታል፡፡ ከጥቂት ምርመራ በኋላ ወይ በዕድሜው፤ ወይ በጾታው፤ ወይ በትምህርት ደረጃው፤ ወይ በመጣበት ሀገር፤ ወይ መጨረሻ በወጣበት ሰዓት የመጀመሪያ ሰው እንደሆነ ሲረጋገጥ ‹‹ በዚያ ሰዓት ለመግባት የመጀመርያው የሰባ ዓመት ዓዛውንት እንደሆነ ይዘገባል :: ታዲያ የናዖድን ፅሁፉን አንብቤ ስጨርስ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “በእኛ ቤት ታሪክ ውስጥ ሁለተኛ ልጅ በመሆን የመጀመሪያው ነኝ” ያለው ትዝ አለኝና ማሪኝ አሜሪካ አልኩ በልቤ::

ኮንጎ - የጉዞ ማስታወሻ ፪

ከሰሞኑ አንድ ምሽት ላይ ከኪንሻሳ ወጣቶች ጋር የባጥ የቆጡን ሳወጋ ነበር፡፡ እንደአብዛኛው የሀገሪቱ ወጣቶች ሁሉ የአለም መጨረሻው ፈረንሳይ ድምበር ከሚመስላቸው ከእነዚህ ጓደኞቼ አንዱ ታድያ ድንገት በጨዋታው መሃል ስለ ኢትዮጵያ ሲያነሳ ቀልቤን ሰበስቤ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ሲጓዝ በአዲስ አበባ በኩል ትራንዚት አድርጎ እንደነበር እና የአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ እጅግ ዘመናዊ እንደሆነ በአግራሞት ተናገረ፡፡ እኔም አጋጣሚውን በመጠቀም ኢትዮጵያ እንዴት እያደገች እንዳለች ለተቀሩት ማስረዳት ቀጠልኩ፡፡

ሶስት ቀናት ሶስት ነገሮች (Aug 23, 2012)

(ባለፉት ሶስት ቀናት እየሁ ሰማሁ ታዘብኩ) 1.       ክፉም ሆነ ደግ፣ ደሃም ሆነ ሃብታም፣ ታሪክ ሰራም አልሰራም፣ ማንም ከሞት አያመልጥም፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ህልፈት አይኑ ያልደረቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ይኸው ጠቅላይ ሚኒስትሩንም አጣ፡፡ ባዶ ቤት ባዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ባዶ ቤተ መንግስት   . . . ታሪክ ግን ብቻውን ቀረ፡፡ መልካም ስራቸውን እና ጉድለቶቻቸውን ገፅ በገፅ ይዞ ታሪክ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ብቻውን ቀረ፡፡ 2.      የስራ ባልደረባዬ ለዚች ሀገር (ዲ.ሪ. ኮንጎ) እንደእኔው እንግዳ ነው፡፡ ብዙ አፍሪካ ሀገሮች ላይ ንግድ ሰርቷል፡፡ እንደ ዲ.ሪ. ኮንጎ አይነት ለቢዝነስ ምቹ ሀገር የትም አይገኝም አለኝ፡፡ ምክንያቱን ስጠይቀው እንዲህ የሚል አስገራሚ መልስ ሰጠኝ "ህግ የሌለበት ሀገር ስለሆነ"፡፡ 3.      ሮበን ቫን ፐርሲን የገዛው ትልቁ ማንቸስተር ዩናይትድ ተሸነፈ፡፡ ያስቃልም ያሳዝናልም፡፡ የግድ ነው፡፡ ሶስት ነገሮች ሳይከሰቱ ሶስት ቀኖች አያልፉም፡፡

እኛ እጅ እናወጣለን - እግዚዓብሔር ይመርጣል

Image
ይህችን የጥንት ቤ/ክ ባሰብኩ ቁጥር ልቤን አንዳች ነገር ወደታች ይጫነኛል፡፡ የሀዘን ስሜት ይከበኛል፡፡ የመንግስተ ሰማይ ተምሳሌት የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ በችግር ተይዛ ስታጣጥር መመልከት እጅግ ያሳምማል፡፡ ለብዙዎች የመፍትሔ ምንጭ የሆነች ቤ/ክ ራሷ ተቸግራ፣ ብዙዎችን ያከመች ቤ/ከ ራሷ ታምማ፣ ታላላቅ ሰዎችን ያፈራች ቤ/ክ ለራሷ የሚሆን ወሳኝ ሰው አጥታ ማየት የእውነትም ይጎዳል፡፡

ዜና ነገ ፩

የግብርና ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ለቀቁ፡፡ ሰኔ 29፣ 2015ዓ.ም (በኢትዮ. አቆጣጠር):- በትላንትናው ዕለት ለተወካዮች ም/ቤት የአመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የግብርና ሚስትሩ የተከበሩ አቶ ብርሃን ባልቻ ሪፖርቱን ባቀረቡ ማግስት ስልጣናቸውን የመልቀቃቸውን ምክንያት ሲገልፁ "ሪፖርቱ ገበሬው በሚገባ ተጠቃሚ እንዳልነበር ያሳያል ስለዚህም የታቀደውን ያህል ልንፈፅም ስላልቻልን በፍቃዳችን ቦታውን ለሌሎች ማስረከብ ይኖርብናል" ሲሉ ለሪፖርተራችን ገልፀ ዋ   ል፡፡ የኢትዮጵያ አረጋውያን ከክፍያ ነፃ ሆኑ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም (በኢትዮ. አቆጣጠር):- በጡረታ የተገለሉ እና በጦር ሜዳዎች ላይ የተካፈሉ አረጋውያን ከመብራት፣ ውሃ፣ ህክምና እና የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ነፃ መሆናቸውን የሚያበስረው አዋጅ ትላንት ጸደቀ፡፡ ለረዥም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ አዋጅ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡ ዜና ነገ - እሺ! መፅሔትን እናዘጋጅ በነበረ ጊዜ በፍቅር እፅፋት የነበረች አነስተኛ አምድ ነች፡፡ በነገይቱ ብሩህ ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት የምመኘውን የምፅፍበት ነፃ ግዛቴ ነው::

ኮንጎሊዝ - የጉዞ ማስታወሻ

Image
የፓትሪስ ሉሙምባ ሃገር   ዲ.ሪ.ኮንጎ ዋና ከተማ የሆነችው ኪንሻሳ እብድ ያደረበት ቤት እንደመሰለች ይኸው ዛሬም ከንጋት ተገናኝታለች፡፡ ካለፈው ሳትማር፣ ከትላንት ሳትለወጥ ትላንት እንዳየናት ይኸው ዛሬም ከነአደረ ፊቷ ፀሀይ ትሞቃለች፡፡ አንዳንዴ ቤቴ ከቢሮዬ ብዙም ባለመራቁ ደስ ይለኛል፡ ምክንያቱም የዳይመንድ ሃብታቸው እየተዛቀ ወደ ምዕራባውያን የሚጋዝባቸውና የበይ ተመልካች ሆነው ከድህነት ጋር በፍቅር የወደቁ ሰዎችን ለረዥም ሰዐት ማየት ያሳምማልና፡፡ የመኪናውን ግርግር አልፌ ራመድ ራመድ እያልኩ ቢሮዬ ገባሁ፡፡

ዳግም ትንሳዔ???

Image
የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጤንነት በተመለከተ ባለፉትን አርባ አምስት ቀናት ይዘገቡ የነበሩ ዜናዎች እና ከወዲህ ወዲያ የተሰነዘሩት አስተያየቶች እርስበርሳቸው የተጣረሱ ከመሆናቸው ባሻገር የብዙ ለውጥ ፈላጊዎችን ደም ሞቅ ያደረገ ሁኔታ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ነፃ የመተንፈሻ ሚዲያ ያጣው የኢትዮጵያ ህዝብም በየፊናው ሆኖ የየራሱን ስሜትና ምኞት ባገኘው የማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ መለጠፉን ተያይዞታል፡፡ አንዱ አዋቂ "ጠ/ሚሩ ከሞቱ 2 ሳምንት አለፋቸው" ሲል ሌላኛው አዋቂ ደግሞ "ንጉሳችን በድል አ/አ ገቡ" ይላል፡፡ አንደኛው የዜና አውታር "ጠ/ሚሩ ከጭንቅላት ጋር የተገናኘ ህመም ይዟቸዋል" ሲለን ሌላኛው ከመቅፅበት "የለም እሳቸውን ካልጋ ያስተዋወቀው የቆየ የሆድ ህመማቸው ነው" ይለናል፡፡ በተለይ ፌስቡክ እና ትዊተር ድረ ገፆች የተቻላቸውን ያህል የየሰውን ስሜት ሲያስተጋቡ ከረመዋል፡፡ ከአንዴም ሶስት ጊዜ ህልፈታቸው በደማቅ አራት ነጥቦች ታጅቦ ታውጇል፡፡ ያንኑ ያህል ግዜም ባይኔ በብረቱ አይቻቸዋለሁ በሚመስል ድፍረት "ሰውየው አዲስ አበባ ምኒልክ ቤ/መ ውስጥ ጋቢ ደረብ አድርገው ሶፋቸው ላይ ጋደም ብለው ሲ ኤን ኤን ከፍተው ዘ ኢኮኖሚስትን እያነበቡ አጃ ነገር እየጠጡ ነው" ያለም አልጠፋም፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እንደሰከረ ሰው ከመዘላበድ ውጪ አንድም የመንግስት አካል በግልፅ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት ማብራርያ መስጠት አልደፈሩም፡፡

አጫጭር ትንፋሾች ፪

ድንገት ነቃ፡፡ የተጀቦነበትንም የፍልስፍና ድሪቶ ከላዩ ገፈፍ አድርጎ አይኑን የሚወጋውን ብርሀን ሊቋቋም እየሞከረ አለምን በግርማሞት መንፈስ አያት፡፡ ዙርያ ጥጉንም ሲገረምም አንዳችም ነፍስ ጎኑ የለም ቢሆንም ብዙም አልተደነቀም፡፡ ምክንያቱም የኔ የሚላቸው ነፍሶች ዞረው ለአለም አግዘው ሲያቆስሉት በተደጋጋሚ ታዝቧልና፡፡ እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው ወፋፍራም  ግን አጫጭር  ትንፋሾች ጉሮሮውን እየቧጠጡት ሳያውቀው እንዲህ የሚል ድምፅ ያወጣው " . . . ይሻለኛል ችጋር፡፡ ከመቶ እጥፍ በላይ ርሃብ ይሻኛል፡፡ ቁርበቴ ገርጥቶ አጥንቶቼ ገጠው ብውል፣ ባድር፣ ብኖር ይሻለኛል፡፡ በቁራሽ እንጀራ እጦት አንጀቴ ተላውሶ በችንጋር አለንጋ ብጠበስ ብቆላ ለእኔ ይሻለኛል፡፡ ጉንጭ ውሃ አጥቼ ምላስ ከትናጋዬ ቢጣበቅ ከንፈሮቼም ደርቀው ኩበትን ቢያስንቁ እመርጣለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ስለ ተስፋ ይሆናል፡፡ ተስፋ አጥቼ ከምኖር አለም ሁሉ ብትቀርብኝ አይጎዳኝም፡፡ ያለ ተስፋ ከመባዘን፣ ሞት የጀግና ዕረፍት ነው ለእኔ፡፡ ተስፋን ከማጣ የምበላው እህል ባጣ እንኳ ግድ አይለኝም እኔ፡፡ ያለ ገንዘብ መኖር እችላለሁ፣ ያለ ተስፋ ግን እስትንፋስ የሌለኝ ደረቅ እንጨት ነኝ፡፡ " ተመልሶ ተጠቅልሎ ተጋደመ እኔም አልቀሰቀስኩትም:: (ኪንሻሳ - ዲ.ሪ ኮንጐ )

ይቅርታ

Image

አጫጭር ትንፋሾች ፩

በተዘበራረቁ ዕውነታዎች፣ በኑሮ ዳገት እና ቁልቁለት፣ በነፍስ አልባ ንጋት እና ጭለማ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ በዚህች አለም ጫጫታ መሀል ድንገት የሚያነቃው ቢኖር የብቸኝነት የጣት ዕሩምታ ብቻ ነው፡፡ ስነ ኑሮ ብቸኝነትን የቂም ጎጆ፣ የበቀልም መንደርደሪያ ይለው ይሆናል እሱ ግን ከዚህ የተለየ ምናልባት የተሸለ ትርጉም ለብቸኝነቱ ይሰጣል፡፡ በብቸኝነቱ ለጊዜውም ቢሆን ከስጋዊ ጭንቀቱ ርቆ በህሊናው ጫካ ይመንናል፡፡ እንጦጦ አናት ላይ ቤቱን እንዳቆመ ጎበዝ በጊዜ አናት ላይ ሆኖ አላፊ አግዳሚውን ይታዘባል፡፡ ውስጡ ዝም ይልና በቅፅበት፣ በአንዳፍታ ብልጭታ መጪ ህይወቱን ይገምታል፣ ያለፈውን ይገመግማል፡፡ ብቻውን የሚሆንበት ጊዜ እያጣ በሔደ ቁጥር ምኞቶቹም ከጊዜ  ባላነሰ ፍጥነት ሲነጉዱ ያያቸዋል፡፡ የእርሱ አለም ደግሞ ከምኞት ይጀምራል፡፡ ጥሬ ምኞቶቹን ያለገደብ ከመንገድ ዳርም ቢሆን ያጭዳቸዋል እቅዶቹን ወደ ህይወት ለመዘርዘር ግን ጥሬ ምኞቶቹን ዳግም በብቸኝነት ውስጥ ማመንዠክ ይኖርበታል፡፡ "አሊያማ ሳሩን ብቻ እንዳየው በሬ ወይንም ካፍንጫው ጫፍ ርቀት በላይ ማየት እና ማስተዋል እንደተሳነው ጎረምሳ መሆኔ ነው" እያለም ይጨነቃል፡፡ እናም ፍቀዱለት በብቸኝነት አለም ይናውዝ ዘንድ አትከልክሉት፡፡ (ኪንሻሳ - ዲ.ሪ ኮንጐ )

ለምን ሀብታም አልሆንኩም?

Image
ከታክሲ ሾፌሩ ጀርባ ሁለት ወጣቶች ተቀምጠው ነበር፡፡ እኔ ከነሱ ኋላ ባለው ወንበር ላይ ሆኜ ስለ መድረሻዬ እንዲሁም አሁን በውል ስለማላስታውሳቸው ነገሮች አሰላስላለሁ፡፡ ከነዚህ ወጣቶች ውስጥ በእኔ ትይዩ ፊት ለፊት ያለው አንደኛው በመደነቅ እና ለማውራት በመቸኮል አይነት ስሜት እየተወራጨ ሲያወራ ሌላኛው ከናፍሮቹን መክደን እንዳለበት እንኳን ረስቶ በትኩረት አፍጥጦ ያዳምጠዋል፡፡ የወሬያቸው ፍሬ ጉዳይ አንድ በቅርብ የሚያውቁት ሰው በማይታመን ፍጥነት እንዴት ሀብታም እንደሆ ነበር፡፡ 

ZUFAN

Image
Dear Readers, This is my first post and i am very delighted to see you here. Today, i would like to present you a graphical expression called "ZUFAN". Please feel free to comment or share your opinion about it. Stay blessed