Popular posts from this blog
እኔ እግዚአብሔር እና ስሜ
በጭለማው መሃል ድንገት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማብሪያ ማጥፊያውን ተጭኖ ጭለማውን ገሰሰው፡፡ አናቴ ደንግጣ እያማተበች በዚያ ለሊት የሚያፈጥባትን ሰውዬ መልሳ ትመለከተዋለች፡፡ “ምንድነው ይሔ?” አላት ሆዷን በሌባ ጣቱ እየጠነቆለ፡፡ እንደመተንፈስ አለችና “እኔንጃ” አለች ፊቱን ላለማየት አቀርቅራ፡፡ “እኔንጃ? ምንማለት ነው እኔንጃ? ኪኒን እንድትወስጂ ተስማምተን እየዋጥሽ አልነበር እንዴ?” በዚያ ፀጥ ባለ ሌሊት የእርሱ ድምፅ ብቻውን እንደመብረቅ ይጮሃል፡፡ “አዎ ኪኒኑንማ እየዋጥኩ ነው” አሁንም እንዳቀረቀረች ነው፡፡ “እና?!?!?” በይበልጥ አምባረቀ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ የምትችል አልመስል አላት ቢመታትም ጠንካራ ክንዱን ለመቻል ተዘጋጅታ “እንግዲህ ኪኒኑ አልሰራልኝም ማለት ነው ያለዚያማ እንዴት ልፀንስ እችላለሁ?” አለችው ተኮሳትራ፡፡ እንግዲህም ይህ ቅፅበት ነበር ለእኔ የህይወት መጀመርያ ለወላጆቼ ደግሞ የመጨረሻዋ ቀን የሆነችው፡፡ አቶ “አባት” እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ የሰውና የጊዜ ክፉ የገጠማት እናቴም እኔን በሆዷ የሆነውን ሁሉ በልቧ ይዛ ብቸኛ ሆነች፡፡ አላማዬ የህይወት ታሪኬን ልነግራችሁ አይደለም የስሜን አመጣጥ ለማብራራት ይሔን ታሪክ መንገር ስላስፈለገኝ እንጂ፡፡
አቦነሽ አድነው “አርቲስት” የሚለው መጠርያ ይገባታል?
ቀደም ሲል በተለየ ቅላፄዋና በባህል ሙዚቃዎቿ የምናውቃት አቦነሽ አድነው “ከዚህ በኋላ ዓለም ከአንደበቴ በሚወጣ ዘፈን አትደንስም ይልቁንስ ጩኸቴ፣ ቅኔ እና ዜማዬ የምስጋና ብቻ ነው” ብላ አዲስ የመዝሙር ስራዎቿን ይዛ ሰሞኑን ብቅ ማለቷ የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ሲያነጋግር የሰነበተ ጉዳይ ነበር፡፡ መቼም ሰው ከአካባቢ ተፅንዖ፣ ከዓለም ዳንኪራ፣ ከከንቱ ውዳሴና ጭብጨባ አምልጦ ሁለመናን ለፈጣሪ ሲሰጥ ማየት መንፈሳዊ ቅንዓት ከማሳደሩም በላይ ያበረታል፡፡ ይህን ስል ግን ዓላማዬ ያልተገባ የሰው ምስጋና ለአቦነሽ ለመስጠት ወይንም ብላቴናዋን ዘማሪት “ቅድስት” ብሎ ለመጥራት አይደለም፡፡

Its beautiful
ReplyDelete