ደህና ሁኚ Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps - August 07, 2019 የተሳሰርንበትን ገመድ ከበጠስሽው ዘንዳ፣ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። ገመድ የለም ከደረቴ፣ ያሰርኩበት ሲባጎም የለምና ከእጄ ሂጂ ብረሪ ክንፎችሽን ዘረጋግተሽ ተንጠራሪ፣ ነፃ ነሽና ፈንጥዢ። የት ሄደች ካሉኝ ፈታኋት እላቸዋለሁ። Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
ዜና ነገ ፩ - August 15, 2012 የግብርና ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ለቀቁ፡፡ ሰኔ 29፣ 2015ዓ.ም (በኢትዮ. አቆጣጠር):- በትላንትናው ዕለት ለተወካዮች ም/ቤት የአመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የግብርና ሚስትሩ የተከበሩ አቶ ብርሃን ባልቻ ሪፖርቱን ባቀረቡ ማግስት ስልጣናቸውን የመልቀቃቸውን ምክንያት ሲገልፁ "ሪፖርቱ ገበሬው በሚገባ ተጠቃሚ እንዳልነበር ያሳያል ስለዚህም የታቀደውን ያህል ልንፈፅም ስላልቻልን በፍቃዳችን ቦታውን ለሌሎች ማስረከብ ይኖርብናል" ሲሉ ለሪፖርተራችን ገልፀ ዋ ል፡፡ የኢትዮጵያ አረጋውያን ከክፍያ ነፃ ሆኑ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም (በኢትዮ. አቆጣጠር):- በጡረታ የተገለሉ እና በጦር ሜዳዎች ላይ የተካፈሉ አረጋውያን ከመብራት፣ ውሃ፣ ህክምና እና የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ነፃ መሆናቸውን የሚያበስረው አዋጅ ትላንት ጸደቀ፡፡ ለረዥም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ አዋጅ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡ ዜና ነገ - እሺ! መፅሔትን እናዘጋጅ በነበረ ጊዜ በፍቅር እፅፋት የነበረች አነስተኛ አምድ ነች፡፡ በነገይቱ ብሩህ ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት የምመኘውን የምፅፍበት ነፃ ግዛቴ ነው:: ሙሉውን አስነብበኝ »
እኔ እግዚአብሔር እና ስሜ - October 05, 2012 በጭለማው መሃል ድንገት ተስፈንጥሮ ተነሳና ማብሪያ ማጥፊያውን ተጭኖ ጭለማውን ገሰሰው፡፡ አናቴ ደንግጣ እያማተበች በዚያ ለሊት የሚያፈጥባትን ሰውዬ መልሳ ትመለከተዋለች፡፡ “ምንድነው ይሔ?” አላት ሆዷን በሌባ ጣቱ እየጠነቆለ፡፡ እንደመተንፈስ አለችና “እኔንጃ” አለች ፊቱን ላለማየት አቀርቅራ፡፡ “እኔንጃ? ምንማለት ነው እኔንጃ? ኪኒን እንድትወስጂ ተስማምተን እየዋጥሽ አልነበር እንዴ?” በዚያ ፀጥ ባለ ሌሊት የእርሱ ድምፅ ብቻውን እንደመብረቅ ይጮሃል፡፡ “አዎ ኪኒኑንማ እየዋጥኩ ነው” አሁንም እንዳቀረቀረች ነው፡፡ “እና?!?!?” በይበልጥ አምባረቀ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ የምትችል አልመስል አላት ቢመታትም ጠንካራ ክንዱን ለመቻል ተዘጋጅታ “እንግዲህ ኪኒኑ አልሰራልኝም ማለት ነው ያለዚያማ እንዴት ልፀንስ እችላለሁ?” አለችው ተኮሳትራ፡፡ እንግዲህም ይህ ቅፅበት ነበር ለእኔ የህይወት መጀመርያ ለወላጆቼ ደግሞ የመጨረሻዋ ቀን የሆነችው፡፡ አቶ “አባት” እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ የሰውና የጊዜ ክፉ የገጠማት እናቴም እኔን በሆዷ የሆነውን ሁሉ በልቧ ይዛ ብቸኛ ሆነች፡፡ አላማዬ የህይወት ታሪኬን ልነግራችሁ አይደለም የስሜን አመጣጥ ለማብራራት ይሔን ታሪክ መንገር ስላስፈለገኝ እንጂ፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ »
Comments
Post a Comment